About Us
Home
About Us
Establishment:
Inspired by filling the gap that existed in publishing content about the Horn of Africa with Amhara perspectives.
Core Values:
Truth, Integrity, and Accountability.
Objectives:
To publish impactful content that:
- enlightens and corrects historical and cultural inaccuracies,
- indicate the best way forward, and
- fill the gap that exists in materials for policy makers with the view to enhance the lives of ordinary citizens in the region.
Who are behind Horn Horizons?
Professionals in various fields, committed to serve their community and the wider region through publication, creation of platforms for discussion and education
Horn Horizons:
- is incorporated with the Government of Washington DC in March 2024;
- is incorporated as a non-profit – pending a 501(c)(3) status;
- is administered by nine board of directors;
- will be financed by member contributions, sponsorships, and sales of printed materials; and
- volunteers will form the bulk of its workforce, with an exception of perhaps a few staff to be employed – given financial resources
Planned activities of Horn Horizons:
- Publications: Journal of Amhara Studies – first journal, perhaps more will come; Books – textbooks, research monographs, conference proceedings, and biographies – as necessary;
- Conference organization (both online and face-to-face); and
- Other activities, as required.
አመሠራረት፤
የሆርን ሆራይዘንስ መመስረት መነሻው፣ ስለ አፍሪካ ቀንድ በሚወጡ የህትመት ውጤቶች ላይ በአማራ እይታ (Amhara perspectives) የተቃኙ ይዘቶችን በማቅረብ ረገድ የሚታየውን ጉልኅ ክፍተት ለመሙላት የነበረው አስፈላጊነት ነው።
መሠረታዊ እሴቶች፤
- ታማኝነት (Integrity)
- ተጠያቂነት (Accountability)
- ትምህርት (Education)
ዓላማዎች፤
ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ይዘቶችን በማሳተም የሚከተሉትን ግቦች ማሳካት፦
- ታሪካዊና ባህላዊ ስህተቶችን ማረምና ግንዛቤ ማስጨበጥ።
- የተሻለውን ቀጣይ መንገድ ማመላከት።
- ለፖሊሲ አውጭዎች የሚያገለግሉ ግብዓቶችን በማቅረብ የሚታየውን ክፍተት መሙላት፤ ይህም በአካባቢው የሚገኙ ተራ ዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል በማለም ነው።
ከሆርን ሆራይዘንስ ጀርባ ያሉት እነማን ናቸው?
በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሙያዎች ሲሆኑ፣ ማህበረሰባቸውንና ሰፊውን ቀጠና በህትመት፣ ለውይይት የሚሆኑ መድረኮችን በመፍጠርና በትምህርት ለማገልገል የተነሳሱ ናቸው።
ስለ ድርጅቱ፤
- በዋሽንግተን ዲሲ መንግሥት ሥር በመጋቢት ወር 2024 (እ.ኤ.አ) ተመዝግቧል።
- እንደ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት (non-profit) የተመዘገበ ሲሆን የ 501(c)(3) የግብር ነፃ መብት ፈቃድ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።
- በዘጠኝ የቦርድ አባላት ይተዳደራል።
- በአባላት መዋጮ፣ በስፖንሰርሺፕ እና በታተሙ ቁሳቁሶች ሽያጭ ይደገፋል።
- አብዛኛው የሥራ ኃይል በፈቃደኞች የሚሸፈን ሲሆን፣ እንደ ፋይናንስ አቅሙ ጥቂት ቋሚ ሠራተኞች ሊቀጠሩ ይችላሉ።
በሆርን ሆራይዘንስ የታቀዱ ተግባራት፤
- ህትመቶች፤ የዓማራ ጥናት መጽሔት (Journal of Amhara Studies) – የመጀመሪያው መጽሔት ሲሆን ወደፊት ሌሎችም ሊታከሉ ይችላሉ።
- መጻሕፍት፤ የመማሪያ መጻሕፍት፣ የምርምር ጥናቶች፣ የጉባኤ ውሎዎች እና የሕይወት ታሪኮች እንደ አስፈላጊነቱ ይታተማሉ።
- የጉባኤ ዝግጅቶች፤ በአካልም ሆነ በበይነ መረብ (online) የሚካሄዱ ጉባኤዎችን ማደራጀት።
- ሌሎች ተግባራት፤ እንደ አስፈላጊነቱ የሚከናወኑ ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎች።